Financial Aid/የገንዘብ ድጋፍ

Procurement Technical Assistance Center (PTAC)/ከመንግስት ስራውን በኮንትራት ወስዶ ለመስራት ይረዳል
ይህ ቢሮ ትናንሽ እና ትላልቅ የንግድ ተቋማት ከፌደራል እና ከስቴት መንግስታት ጋር እንዴት መነገድ እንደሚችሉ በነጻ ያሰለጥናል ፡ ይመክራል ፡ መንገዱንም ያሳያል።ንግዱ ኮንትራት በመውሰድ በጨረታ የሚካሄድ ሲሆን በቀጣይንትም ኮንትራቱን የማሸነፊያ ዘዴዎችን ያመለክታል።

Candid Foundation/ካንዲድ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ ይህ ድርጅት ለለጋሽ እና ልገሳውን ለሚቀበሉ ድርጅቶች ይጠቅማል
ተለጋሽ ድርጅቶች ትርፋማ ያልሆኑ ድርጅቶች መሆን አለባቸው።የተለያዩ በጎ አድራጊ ድርጀቶች ገንዘብ መለገስ ሲፈልጉ ወደ ካንዲድ ፋውንዴሽን መጥተው ይመዘገባሉ።የልገሳ ገንዘብ የሚቀበሉ ድርጅቶችም መስፈርታቸውን የሚያሟሉት ጋር በማመልከት የገንዘብ ልገሳውን ይቀበላሉ።

SBA Federal Contracting & Procurement/የትናንሽ ንግድ ተቋማት አስተዳደር
ከመንግስት ስራውን በኮንትራት ወስዶ ለመስራት ትናንሽ የንግድ ተቋማት የንግድ ስራቸውን ለመጀመር እንዲያስችላቸው የገንዘብ ብድር ይሰጣል።የንግድ ትቋማቱ ለሚፈልጉት የመረጃ እና የምክር ድጋፍ በአቅራቢያቸው ኮሚውኒቲ ናቪጌተርስ በመመደብ እርዳታ ይሰጣል።በተጨማሪም ከመንግስት የኮንትራት ስራ ወስደው እንደሚሰሩ ያስረዳል ፤ ያሰለጥናል።

Grants.gov/ግራንትስ ዳት ጋቨ ትርፋማ እና ትርፋማ ላልሆኑ ድርጅቶች
ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበት መንግስታዊ ድህረ ገጽ ነው።በአብዛኛውን ጊዜ ገንዘብ ለጋሹ መንግስት ሲሆን እንዲስሩለት ያቀዳቸውን ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ለማሳካት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ነው።