Scholarships & Grants/ስኮላርሺፕ እና የገንዘብ ድጋፍ
የዩኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የመጀመሪያ ዲጊሪያቸውን ለሚሰሩ የኮሌጅ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ወይም ኢንተርንሺፕን በውጪ ሀገር ለመማር ለጊልማን ስኮላርሺፕ ማመልከት ይችላሉ ሲል አስታወቀ።ይህን ስኮላርሺፕ የሚቀበሉ ተማሪዎች የፔል ግራንት እርዳታ የተቀበሉ መሆን አለባቸው።እንዲሁም ይህ ስኮላርሺፕ ለሰመር ፡ ለፎል እና ለስፕሪንግ አንዲሆን የተዘጋጀ ሲሆን ሙሉ ወጪን ማለትም የጉዞ ፡ የቤት ፡ የምግብ ፡ የትምህርት እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ይሸፍናል። The […]
ከትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ጊዜ የሚሰጥ የትምህርት እዳ ቅነሳ ማመልከቻው ተከፍቷል።ይህ ዕዳ ቅነሳ የሚሰራው ከጁን 30 በፊት የትምህርት እዳ ላላቸው ተማሪዎች ሲሆን በገቢያቸው መጠን የሚሰጥ ነው።ፔል ግራንት ከዚህ በፊት ለተቀበሉ ገቢያቸው ታይቶ እስከ $20000 እና ፔል ግራንት ላልተቀበሉ ደግሞ እስከ $10000 የእዳ ቅነሳ ድረስ ይሰጣቸዋል።በተዘጋጀው መስፈንጠሪያ አማካኝነት ለዕዳ ቅነሳው ማመልከት ትችላላችሁ። ማሻሻያ፡ ይህ የተማሪዎች እዳ ቅነሳ […]

FAFSA Application/ፋፍሳ ማመልከቻ ፋፍሳ
በፌደራል መንግስት የሚሰጥ የኮሌጅ ትምህርት ድጋፍ ሲሆን የስኮላርሺፕ ፡ የግራንት ፡ የብድር እና የወርክ ስተዲ ፕሮግራም አለው።በየአመቱ ኦክቶበር 1 ቀን የፋፍሳ ማመልከቻ ይከፈታል ነገር ግን መዝጊያው በየስቴቱ እና በፌደራል መንግስት ይለያያል።

School Benefits/ለትምህርት ቤት ጥቅማ ጥቅሞች
ቤኒፊትስ ዳት ጋቨ ለትምህርት ቤት ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ይረዳል።ከዚያም በላይ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለምሳሌ የስራ ፡ የጤና ፡ የንግድ እና የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፎችን እንድናገኝ ያግዛል።

Scholarship America/ስኮላርሺፕ አሜሪካ
የተለያዩ ስኮላርሺፖችን ሰብስቦ የያዘ ሲሆን በአብዛኛውን ስኮላርሺፕ የሚመጣው ከጥቅምት እስከ ማርች ወር ነው።የራሳችሁን እካውንት ከከፈታችሁ በኋላ ዳሽ ቦርዳችሁ ላይ ለእናንተ የሚስማማ የስኮላርሺፕ ድጋፍ ሰብስቦ ያመጣላችኋል።

Nursing Expansion Grant Program/የነርሲንግ ፕሮግራም ማስፋፊያ ግራንት
የነርሲንግ ሙያ ስልጠና በሚሰጡ ድርጅቶች በመቀጠር የነርሲንግ እውቀት እና ችሎታችንን ማሳደግ እንችላለን።እኛ ማድረግ ያለብን የ H-1B ግራንት አሸናፊ ድርጅቶችን ፈልገን መቀጠር ነው።ድርጅቱ በስሩ ያሉ ነርሶችን እና የነርስ ረዳቶችን በነጻ በሙያ እያሰለጠነ ያሳድጋል።