Tax/ግብር

U.S. Women’s Chamber of Commerce/የአሜሪካ የሴቶች ንግድ ምክር ቤት

National Women’s Business Council/ብሄራዊ የሴቶች የንግድ ምክር ቤት

Tech Girls/ሴት ልጆች እና ቴክኖሎጂ

በአለም ዙሪያ ከተለያዩ ሃገሮች የተመረጡ ሴቶች ልጆች ከ 15-17 ዓመት እድሜ ክልል ያሉትን ወደ አሜሪካ ቨርጂኒያ ቴክ ዪኒቨርሲቲ ለ 25 ቀናት በማምጣት የቴክኖሎጂ አና የኮምፒውተር ካምፕ እንዲሳተፉ ያደርጋል።በአጠቃላይ  የሳይንስ ፡ ቴክኖሎጂ ፡ ምህንድስና እና ሂሳብ ላይ ያተኮረ።

Girls for Technology/ሴት ልጆች ለቴክኖሎጂ

ገርልስ ፎር ቴክኖሎጂ ሴቶች ልጆችን በስራ ክህሎት ፡ በፈጠራ ስራ ፡ እና በወጣቶች የመነሳሳት ስራ ላይ ለማበረታታት የተቋቋመ ድርጅት ነው።ሴቶች በሳይንስ ፡ በቴክኖሎጂ ፤ በምህንድስና እና በሂሳብ ዕውቀት እና ችሎታ ከማሳደግ ጋር የንግድ ድርጅት ባለቤቶች እንዲሆኑ ያበረታታል።ይህ ደግሞ የሃብት ክምችትን ይጨምራል።የጥቁሮች የንግድ ድርጅቶች እንዲከፈቱ ፡ እንዲያድጉ እና እንዲስፋፉ የገንዘብ እርዳታ መረጃን ይሰጣል።

SBDC Women Development Center/ኤስቢዲሲ የሴቶች ልማት ክፍል

ኤስቢዲሲ በአሜሪካ መንግስት ስር የሚተዳደር እና በእያንዳንዱ ግዛት ውስጥ መቀመጫውን በስቴት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በማድረግ የሚሰራ ነው። ለትናንሽ የንግድ ተቋማት ንግድን እንዴት እንዲጀምሩ  አንደሚያሳድጉ እና እንደሚያስፋፉ መንገዱን ያሳያል ፡ ያሰለጥናል። ሙያዊ የምክር አገልግሎቶችን በነጻ እንዲያገኙ ያደርጋል።እዲስ የንግድ ተቋማትን ከነባሮቹ ጋር በማገናኘት ልምድ እንዲቀስሙ ያደርጋል። 

Skip to content