We’re hiring passionate Mentors, Tutors, Program Coordinators & Security Officers to empower youth in Maryland, Washington D.C., Virginia Apply now and make a difference!
Life Youth Mentorship & Tutoring (LYMT) – Second Batch Now Open!
After successfully completing our first year LYMT program, we’re excited to welcome our second batch of students! Led by college educated mentors & tutors, LYMT offers academic support, life skills, STEM tutoring, and enriching activities to help youth excel.
Special Offer: Enroll now for just $200/month (was $250) – limited seat only! (Click here)

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የአኩኩሉ ፋሚሊ ቤተሰቦች! የከበረ ሰላምታችን ከያላችሁበት ይድረሳችሁ!

መረጃ እና አጠቃቀሙ

መረጃን ለማግኘት ትኩረት እና ጥረት የሚጠይቅ ስራ ነው።መረጃውን የምናገኝበት ፍጥነትም
ወሳኝነት አለው።በተጨማሪም በመረጃው ውስጥ የተካተቱት ዝርዝር ሃሳቦችም ትኩረት ያሻሉ።እኛ
መረጃውን ካገኘንስ በኋላ ለማን ? እንዴት ? መቼ ? የት ቦታ ? በምን መልኩ? መረጃውን እናስተላልፈው
የሚሉት ሃሳቦች አዕምሮአችንን ውስጥ ሊመላለሱ ይችላሉ።ራሳችን ተጠቅመን ወገኖቻችንን
መጥቀም ደግሞ ስኬታማ የመረጃ አጠቃቀምን ያሳያል።

መረጃዎች ከመንግስታዊ አና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ይወጣሉ።የፖሊሲ ለውጦች እና
ማሻሻያዎች ፤ ህጎች እና አዳዲስ የመተዳደሪያ ደንቦች ፤ የገንዘብ ድጋፎች እና ድጎማዎች እንዲሁም
ዜናዎች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይመጣሉ።መረጃዎች ቢበዙም በየመልኩ ከፋፍሎ መጠቀም ከእኛ
የሚጠበቅ ስራ ነው።

እኛ በእለት እለት ኑሮአችን ተጠምደን ስንውል እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ያመልጡናል።እነኚህን
መረጃዎች የምንፈልግበት ፡ ተጠቅመን ሌሎችን የምንጠቅምበት ጊዜ በአግባቡ አንመድብለትም።ቀኑ
ሳናውቀው ያልቅብናል።በቀኑ መጨረሻም ከድካማችን እፎይ ስንል የሚቀናን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ
ተቀምጠን በማይጠቅሙን መረጃዎች ሰዓታችንን ማባከን ነው።ምናልባትም የሚጠቅመን መረጃ
በማህበራዊ ገጻችን እልፍ ቢል ተገቢውን ትኩረት ላንሰጠው እንችላለን።

በውጭው አለም በምንኖርበት ሃገር የመግባቢያው ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን ካልሆነ
ለመረጃ ማግኘት እና መጠቀም ተጨማሪ እንቅፋት ይፈጥርብናል።በዚህ ሁኔታ መረጃውን ተረድቶ
የሚተርጉም አካል ማግኘት ትልቅ እፎይታ ይሰጣል።በተለይ መረጃዎች ከየአቅጣጫቸው ከምንጫቸው
ተሰብስበው እና ተተርጉመው በማዕከላዊ የመረጃ መድረክ መቅረብ ቢችሉ ለተጠቃሚየዎች
የተቀላጠፈ ፍሬያማ አገልግሎት እንዲያገኙ ይረዳል።

የአኩኩሉ ፋሚሊ በማህበረሰባችን የሚታየውን የመረጃ እጥረት እና የአጠቃቀም ጉድለት በመረዳት
ለወገኖቻችን ይጠቅማል የምንለውን የመረጃ እና የመገናኛ መድረክ ይዘን ቀርበናል።የአኩኩሉ ፋሚሊ
መድረክ ለእናንተ ይበጃሉ በሚላቸው በጤና ፤ በትምህርት ፤ በንግድ እና ገንዘብ አያያዝ እንዲሁም
በስፖርት እና መዝናኛ ልዩ ልዩ መረጃዎች ይዞላችሁ ይቀርባል።መረጃዎችን ከእኛ በመውሰድ እና
ለእኛም በማቀበል መረጃ የማዳረስ ድርሻዎትን ይወጡ።

በመንገናኛ ብዙሃናችን ፡ በፓድካስት ፡ በድህረ ገጻችን ፡ በስልክ ፡ በኢሜል እና በደብዳቤ
መልዕክቶቻችሁን ልትልኩልን ትችላላችሁ።

አብረን እንደግ!!!

ዶ/ር እልልታ ረጋሳ

አኩኩሉ ፋሚሊ

Disclaimer: At Akukuly Family, we gather information from various internet sources to provide valuable insights and resources through our blog. While we strive to ensure the accuracy and relevance of our content, we encourage readers to verify information and consult professional advice where necessary. The views and opinions expressed in our blog posts are those of the authors and do not necessarily reflect the official policy or position of Akukuly Family.

Photo Credits & Concerns All images used on our website are sourced from stock image libraries and are believed to be free for use. However, if you believe any image violates copyright or you have any objection to its use, please contact us at ceo@akukulufamily.com, and we will promptly address the issue or take down the image as requested.
Editorial Staff -Akukulu
Editorial Staff -Akukulu

Akukulu Family is a limited liability company registered in Maryland to create awareness and serve as a mentoring and networking platform for all minority communities

Skip to content